የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ እና ለማዘመን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባቸው በባንክ እንዲከፍሉ የሚያስችል የውል ስምምነት በትናንትናው እለት ተፈራርሟል፡፡ስምምነቱ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል መፈፀሙን ሪፖርተራችን ቃልኪዳን ተስፋዬ በስፍራው ተገኝታ ተከታትላዋች፡፡የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 27ሺ የሚሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ከፍተኛ ፍጆታ ተጠቃሚ ተቋማት እንዳሉትም የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ በተለይም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡