መደበኛ ያልሆነ

የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጠል ገለጸ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በትናንትናው እለት በሮም የተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆዜ ግራዚያኖ ድ ሲልቫ ጋር በተወያዩበት ወቅት ድርጀቱ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጠል ገልጿል።

በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ትብብር በማጠናከር ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለማምጣት ቅድሚያ ተሰጠቶ እየተሰራ መሆኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ገልጸዋል። የቀጠናው ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት ነው ብለዋል።

ሀገሪቱ የምግብ ዋስትና መርሃ ግብሯን ስኬታማ ለማድረግ አነስተኛ ገበሬዎች የሚያጋጥማቸውን የገበያ ትስስር ለመቅረፍ በስፋት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ቀንድ እየተጫወተች ያለውን ሚና ገልጸው፣ በቀጠናው ሰላምን ለማምጣት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን አድንቀዋል።

ብስራት ሬድዮ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት በተላከለት መረጃ መሰረት ዓለም አቀፉ የምግብና እርሻ ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *