መደበኛ ያልሆነ

ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እየተጫወተች ያለውን ሚና አደነቁ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከጣሊያኑ ፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ ጋር በትናንትናው እለት በጣሊያን ሮም በተወያዩበት ወቅት ጣሊያን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እየተጫወተች ያለውን ሚና አድንቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ውህደት እንዲመሰረት እና ቀጠናዊ ሰላም እንዲሰፍን እየተጫወተች ያለውን ሚና በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት በላከው መግለጫ መሰረት ፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እየተጫወተች ያለውን ሚና አድንቀዋል።ለውጡ ከዚህ በላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *