መደበኛ ያልሆነ

ጠ/ሚር ዐብይ አሕመድና ልዑካቸው ከጠ/ሚር ሊ ኬኪያንግ ጋር የኢትዮ ቻይናን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ዙሪያ ተወያየ

ጠ/ሚር ሊ ኬኪያንግ ቻይና ኢትዮጵያ የዜጎቿንና
የኢኮኖሚዋን ደኅንነት ለማስቀጠል የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ አረጋግጠዋል:: ሁለቱ
ጠቅላይ ሚኒስትሮች ይህንኑ ትብብር የሚያጠናክሩ አምስት ስምምነቶች እንዲፈረሙ
አድርገዋል::
የተፈረሙት ስምምነቶችም:
1. የሸገርን ማስዋብና ፕላዛ ፕሮጀክት 12 ኪሎ ሜትር የሚሽፍን የፋይናንስ ስምምነት
2. የቴክኒክ ትብብር ስምምነት
3. ለምግብ ርዳታ ስምምነት
4. ለቤልት ኤንድ ሮድ ማሕቀፍ የአምስት አመት ትብብር እቅድ
5. በቻይና አፍሪካ የትብብር መድረክ (FOCAC) ሥር የሚካሄድ የትብብር መተግበሪያ
የመግባቢያ ሰነድ ናቸው::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *