የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በትናንትናው እለት በኢትዮጵያ የጅቡቲ አምባሳደር እና የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች ቡድን ዲን የሆኑትን አምባሳደር ሙሃመድ እድሪስ ፋራህን በጽ/ቤታቸው ተቀበለው አነጋግረዋል።
ሚኒስትሩ የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ጠቅሰው ኢትዮጲያ ከጅቡቲ ጋር ላላት ግንኙነት ልዩ ቦታ እንዳላት ገልጸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት በላከው መግለጫ መሰረት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ስትራቴጅያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
አምባሳደሩ በበኩላቸው ሚኒስትሩ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በማነጋገራቸው አመስግነው የሀገራቱን ስትሬቴጅያዊ ግንኙነት በሁሉም ዘርፍ አጠናክረው ለማስቀጠል ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ስምኦን ደረጄ