መደበኛ ያልሆነ

በህገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ

ሰላሳ አምስት ሽጉጦች መነሻውን ውጫሌ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ሃይሉክስ ተሽከርካሪ አካል ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞከር ሚያዝያ 23 ቀን 2011 ዓ.ም ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት አዋሽ ኬላ በቁጥጥር መዋሉን በገቢዎች ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲስ ይርጋ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በቁጥጥር ከዋሉት ሽጉጦች 33ቱ የቱርክ ስሪት ያላቸው ሲሆኑ ሁለቱ ማካሮቭ ሽጉጦች ናቸው፡፡

ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ የጫነው ተሽከርካሪ ሹፌር አዩብ አብዲ የተባለ ግለሰብ ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርግም በቁጥጥር ስር መዋሉን አቶ አዲስ ይርጋ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

 

ትንግርት ሙሉጌታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *