መደበኛ ያልሆነ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዩኔስኮ ፌሊኒክስ ሃፌፍ- ቦኒይ የሰላም ሽልማት 2019 አሸናፊ ሆኑ

 

ብስራት ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት በተላከለት መግለጫ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰላምን ለማምጣት፣ ለማስጠበቅና ለማቆየት ላደረጉት አስተዋፅኦ የዩኔስኮ ፌሊኒክስ ሃፌፍ- ቦኒይ የሰላም ሽልማት 2019 አሸናፊ ሆነዋል።

የዩኔስኮ ፌሊኒክስ ሃፌፍ- ቦኒይ የሰላም ሽልማት ከሃያ በላይ አለም አቀፍ ታዋቂ ግለሰቦች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1991 ጀምሮ ሲሰጥ ቆይቷል።

ይህ ሽልማት “ዓለም አቀፍ ግጭቶችን በመፍታት፣ የውይይትን እና ድርድርን ሚና በማጉላትና በመቻቻል፣ በእኩልነትና በመግባባት ሰላም እንዲሰፍን አስተዋፅኦ ላደረጉ ግለሰቦች” ይሰጣል።

 

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *