መደበኛ ያልሆነ

ከስንዴ ግዥ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ይገዙ ዳባን ጨምሮ 10 ሰዎች ክስ ተመሰረተባቸው

ተከሳሾች እንደ ቅደም ተከተላቸው ይገዙ ዳባ ገቢሳ፣ አቶ መንግስቱ ከበደ ደስታ፣ አቶ ሰለሞን
በትረ ገ/ሥላሴ፣ ሰለሞን አይኒማር ካህሣይ፣ ዮሴፍ ራፊሶ ጉዬ፣ ተ/ብርሃን ገ/መስቀል አበራ፣
ትሩፋት ነጋሽ ገብሬ፣ ዘሪሁን ስለሺ ገድሌ እና ጆንሴ ገደፋ ለታ ናቸው፡፡
ተከሳሾች ከ2010 እስከ 2011 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ለገበያ ማረጋጊያ ዓላማ በተፈጸመ
ዓለም አቀፍ የስንዴ ግዥ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ፕሮሚሲንግ ኢንተርናሽናል ለሚባል
ድርጅት ለማስገኘት ወይም በመንግስት ጥቅም ላይ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ በተሰጣቸው
ኃላፊነት መሠረት ሊጠብቁት እና ሊከላከሉት የሚገባቸውን የመንግስትን ጥቅም የሚጎዳ
ተግባር ለመፈጸም በማሰብ ከ1ኛ እስከ 4ኛ የተዘረዘሩት ተከሳሾች የተሰጣቸውን ኃላፊነት
ተጠቅመው በመመርያውና በውሉ መሠረት የሻኪል ኤንድ ካምፓኒ የወጣውን የ400,000 ሜ/
ቶን ስንዴን ባሸነፈበት 96,400,000 የአሜሪካን ዶላር በውሉ መሠረት የጠየቀውን የውል
ማስከበርያ ማቅረቢያ ተጨማሪ ጊዜ ሰጥተው እንዲያስገባ አድርገዋል፡፡
ከ5ኛ እስከ 9ኛ የተዘረዘሩት ተከሳሾች ለ2ኛ ጊዜ የወጣውንና በሦስት አቅራቢዎች አሸናፊነት
የተጠናቀቀውን ጨረታ ከመመርያ ውጪ የቀረበን የአንድ አባል ሀሳብ ምክንያት በማድረግ
የግዥ ኮሚቴ የሀሳብ ልዩነት አለው በሚል ያልተገባ ምክንያት ጨረታውን ያለአግባብ
እንዲሰረዝ በማድረጋቸው የተሰጣቸውን ኃላፊነት ባለመወጣታቻው በወቅቱ ከቀረበው
የ110,786,000 የአሜሪካን ዶላር እና በመጨረሻ ለ400,000 ሜ/ቶን ስንዴ መንግስት
ከከፈለው 115,492,188.00 ዶላር የአሜሪካን ዶላር አንጻር በልዩነት የተከፈለ 4,706,188
ዶላር በመንግስት ላይ ጉዳት እንድደርስ መደረጉን ከክሱ መረዳት ተችሏል፡፡
እንዲሁም 1ኛ ተከሳሽ ግዥዎቹ በአቅራቢዎች መርከብ እንዲጓጓዝ በማድረግ ሃገሪቱ ከመርከብ
ትራንስፖርት ልታገኝ የምትችለውን 5,895,000 የውጭ ምንዛሪ ወይንም 162,786,888 ብር
በማሳጣት፣ 10ኛ ተከሳሽ ፕሮሚሲንግ ኢንተርናሽናል ጋር በስውር በመመሳጠር በመመርያው
መሰረት በወቅቱ እርምጃ ባለመውሰድ 3,675,000 ዶላር ወይም 101,482,920 ብር ጥቅም
እንዲያገኝ በማድረግ ተከሣሾች በሥራቸው ሥልጣን መሰረት ሊጠብቁት እና ሊከላከሉት
የሚገባውን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር በመፈጸም በስንዴ ግዥ ፕሮሚሲንግን ኢንተርናሽናል
የተባለውን ድርጅት ያለአግባብ በመጥቀምና መንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ እንዲሁም
በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የስንዴ፣ የዱቄትና የዳቦ እጥረት እንዲሁም የዋጋ መናር እንዲከሰት
በማድረግ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት የመንግሥት ሥራን በማያመች
አኳኋን መምራት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ተከሳሶችም ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የቀረበባቸውን ክስ በችሎቱ ተነቦ እንዲረዱት ተደርጓል፡፡ በቀረበበው ክስ ላይ ያለቸውን የክስ መቃወሚያ ይዘው ለመቅረብ
ለግንቦት 06 ቀን 2011 ዓ.ም ተቀጥሯል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *