መደበኛ ያልሆነ

ኮ አክሽን መስማት የተሳናቸው መዋዕለ ህፃናት ት/ቤት የመፈራረስ አደጋ ተጋርጦበታል

ት/ቤቱ ለበርካታ መስማት የተሳናቸው ህፃናት አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሄራዊ ማህበር መስራች አቶ ተክለሃይማኖት ደርሶ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

ይህንን ዓላማ በማድረግም በኢትዮጵያ የሚገኙ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች ትምህርትን ለማዳረስ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።

አሁን ላይ ትምህርት ቤቱ የመፈራረስ አደጋ እንደተጋረጠበት የገለፁት አቶ ተክለሃይማኖት ፤ አስከፊ በሚባል ደረጃ ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል።

ማህበሩ የእድሳቱን ወጪ መሸፈን እንደማይችልና ፤ አንዳንድ በጎ ፍቃደኞች እንዲሁም የቀድሞ ተማሪዎች ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኝ ነግረውናል።

ሆኖም ለት/ቤቱ እድሳት ከዚህ በላይ ድጋፍ እንደሚያስፈልግና በመንግስት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ አለመሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስዳደር አሁን ተግባራዊ እያደረገ የሚገኘውን የት/ቤቶች የእድሳትና የጥገና መርሀ ግብር በትምህርት ቤቱም ላይ ተግባራዊ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *