መደበኛ ያልሆነ

የሳዑዲ መራሹ ጥምር ጦር በየመን ስድስት ጊዜ የአየር ላይ ጥቃት ፈፀመ።

በመዲናዋ ሰንዓ ትናንትና ምሽት ስድስት ጊዜ የአየር ጥቃት ስለመሰንዘሩ የሀገር ውስጥ የመረጃ ምንጭ የሆነው አልማስሪያ ዘግቧል።ጥቃቱ ንፁሃን ላይ ያነጣጠረ ስለመሆኑም ተገልፃል።ስለጥቃቱ ተጎጂዎች ግን የተባለ ነገር የለም። የጥምር ቡድኑ ጥቃት ንፁሃንን ተጎጂ ከማድረግ ባለፋ 45 በመቶ የየመንን የመሰረተ ልማት አውታር በማውደም ክፉኛ ሀገሪቱን ጎድቷል።የየመን የፓለቲካ ምክርቤት ሀላፊ ሞሃመድ አል ሃውቲ በጥምር ቡድኑ ውስጥ አባል የሆኑ ሀገራትን የመንን ለመከፋፈል ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም ብለዋል።ከመጋቢት 2015 አንስቶ በቀጠለው የየመን ቀውስ ሳዑዲ የሀዲ ሀይሎችን ወደ ስልጣን ለመመለስ በየእለቱ 2 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ፈሰስ ብታደርግም ውጤት ልታገኝ አልቻለችም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *