መደበኛ ያልሆነ

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ለተማሪዎች ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የደብተር ድጋፍ አደረገ፡፡

ሚድሮክ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የደብተር ድጋፍ አድርጓል፡፡

በተጨማሪም ሚድሮክ ኢትዮጵያ የፊታችን ጳጉሜ 3 ለሚካሄደው ብሄራዊ የኩራት ቀን “አዲስ አበባ ቤቴ ፤ ኢትዮጵያዊነቴ ኩራቴ!” የሚል ፅሁፍ ያረፈበት 100 ሺ ትሸርቶችን አዘጋጅቶ ለከተማ አስተዳደሩ ለማስረከብ ቃል ገብቷል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ለተማሪዎች ላደረገው የደብተር ድጋፍ በተማሪዎች ፣ በወላጆች እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *