መደበኛ ያልሆነ

የ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወደ 11ኛ ክፍል መግቢያ ይፋ ሆነ::

የመደበኛ፣የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች ለወንድ 2 ነጥብና ከዚያ በላይ ለሴት 1 ነጥብ 86 እና በላይ ሆኖ የማታና የግል ተፈታኝ ተማሪዎች በማታው ፕሮግራም ይቀጥላሉ::

ለአካል ጉዳተኞች መስማት የተሳናቸው ለወንድ 1 ነጥብ 86 እና በላይ ለሴት 1ነጥብ 71 እና በላይ እንዲሁም ለዓይነ ስውራን ለወንድ 1 ነጥብ 71 ለሴት 1 ነጥብ 61 እንዲሆን ተወስኗል::

ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች፣አርብቶ አደር አካባቢዎች እና የፀጥታ ችግር የታየባቸው አካባቢዎች ደግሞ ለወንድ 1 ነጥብ 86 ለሴት 1 ነጥብ 71 እንዲሆን መወሰኑን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ሁሉም ወደ 11ኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች የሚመርጡት የትምህርት መስክ በትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታው በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በምርጫ ተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ ብቻ ይሆናል፡፡

ከዚህ በፊት የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት 10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 2 ነጥብ እና ከዚያ በላይ ያመጡ በማታው ፕሮግራም የ11ኛ ክፍል ትምህርታቸውን መቀጠል የሚችሉ መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *