መደበኛ ያልሆነ

የድራማ ጽሁፍ የሚመስለዉ እውነተኛ የአባትና ልጅ አስገራሚ የፉክክር ታሪክ በኢትዮጵያ

በባሌ ጎባ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ሼክ ካሚል አልዬ የ6 ልጆች አባት ናቸዉ፡፡የመጀመሪያ ልጃቸዉን ረመዳን ካሚል ወደ ትምህርት ቤት ለማስመዝገብ ሲሄዱ እኔስ ለምን አልማርም ሲሉ ትምህርታቸዉን ይጀምራሉ፡፡

አባትና ልጅ በጋራ ትምህርታቸዉን መማር ይጀምራሉ፡፡መጀመርም ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ተፎካካሪ ይሆናሉ፡፡እርስ በእርስ ያላቸው ፉክክርን ተከትሎ ከ1ኛ እስከ 10ኛ ክፍል አባት አንደኛ ሲወጡ ልጅ ሁለተኛ፤ልጅ አንደኛ ሲወጣ አባት ሁለተኛ ሆነዉ ይቀጥላሉ፡፡

በ10ኛ ክፍል ማትሪክ አባት 3.6 ሲያመጡ ልጅ 3.8 ያመጣል፡፡እንዲህ የቀጠሉ አባትና ልጅ በ12ኛ ክፍል የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና ልጅ 500 አባት 490 ዉጤት ያመጡና ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ፡፡

አባት ከመዳ ወላቡ ዩኒቨርስቲ በማኔጅመንት ሲመረቁ ልጅ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሀይድሮሊክ ኢንጅነሪንግ ተመርቀዋል፡፡በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ የልጃቸዉ ሰቅሎ መቅረት የከነከናቸዉ አባት በመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ሁለተኛ ዲግሪያቸዉን ሲይዙ ልጅም ሁለተኛ ዲግሪዉን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሁለቱም በዩኒቨርስቲ በመምርነት በመስራት ላይ የሚገኙ ሲሆን ፉክክሩ አላበቃም፡፡ፉክክሩ ጤናማ ሲሆን አንዳቸው ሌላኛውን ለመብለጥ ዘወትር አያንቀላፉም ነበር።

ስምኦን ደረጄ

BisratNews #Ethiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *