መደበኛ ያልሆነየእነብርጋዲዬር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ለጥቅምት 12 ቀን ተቀጠረ፡፡ October 8, 2019October 8, 2019 Tamiru W የእነብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ የምርመራ ጉዳይ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፖሊስ ምርመራ ቡድን የጠየቁት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ረፋድ ባስቻለው ችሎት የመርማሪ ቡድኑ የጠየቀውን የተጨማሪ ቀጠሮ ይግባኝ ውድቅ አደርጓል፡፡ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2012ዓ.ም ድረስም ክስ እንዲመሠርት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡ መርማሪ ቡድኑ ይግባኝ ከጠየቀበት ጊዜ ጀምሮ ተጠርጣሪዎቹ ለ64 ቀናት በማረፊያ ቤት የቆዩ በመሆናቸውና መርማሪ ቡድኑ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ መረጃ እያጣራ ያለ መሆኑን፣ ቀሪ ምስክሮችም ጥቂት መሆናቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ጥቅምት 12 ቀን 2012ዓ.ም ክስ እንዲመሠረት ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን ዘግቷል፡፡ Share this:Click to share on Twitter (Opens in new window)Click to share on Facebook (Opens in new window)Click to share on Google+ (Opens in new window)Like this:Like Loading... Related