መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 24፣2012

በኮሮና የተነሳ የሰላምታ ልውውጥ በእግር!

የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ከተቃዋሚው ፓለቲከኛ ማአሊም ሻሪፍ ሀማድ ጋር በእግራቸው ሰላምታን ሲለዋወጡ የሚያሳይ ምስል ከታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ተለቋል።

አላማው ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ነው የተባለ ሲሆን ዜጎች መተቃቀፍ፣መሳሳምንና እጅ ለእጅ መጨባበጥን ይህ አስፈሪ ጊዜ እስኪያበቃ እንዲያቆሙ የታንዛኒያ መንግስት መክሯል።

በ6 የአፍሪካ ሀገራት ቫይረሱ የተዛመተ ሲሆን ከ3000 በላይ ሰዎችን ህይወት ነጥቋል።

የኮሮና_ቫይረስ ወደ ቱኒዚያ መግባቱ ተሰማ። ከጣሊያን ወደ ቱኒዚያ የመጣው የ40 ዓመቱ ሰው በቫይረሱ የተጠቃ መሆኑ ተረጋግጧል። ቱኒዚያን ጭምሮ በአፍሪካ አልጄሪያ፣ናይጄሪያ እና ግብፅ ኮሮና ቫይረስ ተዛምቷል።

ግብፅ አሸባሪ ነው ስትል በፅኑ ስትፋልገው የነበረውን ሰው የሞት ፍርድ በየነችበት።

ካይሮን ጨምሮ በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች የሽብር ጥቃትን በማስተባበር የሚታወቀው ግለሰብ ሂሻም አሽማዋይ በመባል ይታወቃል።

ግለሰቡ በሊቢያ እ.ኤ.አ በ2018 በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።

#BisratNews #CoronaVirus #Egypt #Tunisia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *