መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 29፣2012

የአፍጋኒስታን መንግስት 5,000 የታሊባን አባላትን ለመፍታት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር መክሯል።

የታሊባን አባላትን ከመፍታታችን በፊት ግን እነዚህ ታራሚዎች መልሰው ታሊባንን ተቀላቅለው ጥቃት ለመፈፀም ቢሞክሩ ምን ማስተማመኛ አለኝ ሲል የአፍጋን መንግስት ጠይቋል።
######

በኮሮና ቫይረስ(Covid 19) ስጋት ዛሬ ከቫቲካን የፀሎት ስነስርዓት በቀጥታ የቪዲዮ ስርጭት ፖፕ ፍራንሲስ ቡራኬ ሰጥተዋል።
######

ከወራት በፊት ግንባታው የተጀመረው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የሲቪል ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የማሽን ተከላው እየተከናወነ ይገኛል።

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የፋብሪካው ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
######

~የአለማችን የመጀመሪያዋ የኮምፒውተር ፕሮግራመር ሴት ናት።
~ደራሲዋና የመብት ተሟጋቿ ሄለን ኬለር የመጀመሪያዋ አይነስውርና መስማት የተሳናት በአርት የባችለር ዲግሪዋን የተቀበለች ሰው ናት።
~ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ የአፍሪካ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ስትሆን ለሁለት የምርጫ ዘመን በፕሬዝዳንትነት አገልግላለች።
######

~አንዲት ሴት በቀን በአማካኝ 20 ሺ ቃላትን ስትናገር ወንዶች 13 ሺ ቃላትን ይናገራሉ።
~አንዲት ሴት በዓመት ከ30 እስከ 64 ጊዜ ስታለቅስ የወንዶች ከ6 የበለጠ አይደለም።
~ወንዶች ከሴቶች በእጥፍ የበለጠ ይዋሻሉ።
~ሴቶች ከወንዶች በበለጠ በአንድ ጊዜ በርካታ ተግባራትን ማከናወን ይችላሉ።
######

~በየ90 ሰኮንድ ልዩነት አንዲት ሴት ከወሊድ ጋር በተያያዘ እክል ህይወቷ ያልፋል።
~አንዲት ሴት እዚህ ምድር ላይ 75 አመታትን ብትኖር በአማካኝ 4 አመታት ከህይወቷ በወር አበባ ዑደት ውስጥ ነች።
~የልብ ህመም ለሴት ልጅ ዋንኛ ገዳይ በሽታ ነው።
~ከ6 ሴቶች አንዷ የጥቃት ሰለባ ነች።
######

በከተማ ዙሪያ የተሰራ ጥናት

አንዲት ሴት በአማካይ ምድር ላይ 75 አመታትን ብትኖር ምን አይነት ልብስን ልልበስ በሚል ውሳኔ ከእድሜዋ አንድ አመት ታጠፋለች።

ሊፒስቲክ ተጠቃሚ ሴቶች በእድሜ ዘመናቸው ከ3 ኪሎ ሊፒስቲክን ይጠቀማሉ።

እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ባለ ተረከዝ ጫማ(Heels)የወንዶች ጫማ ብቻ ነበር።
######

የአለማችን የመጀመሪያው የልቦለድ መፅሀፍ በ11ኛው ክፍለ ዘመን በጃፓናዊቷ ደራሲ ሙራሳኪ ሺኪቡ ተዘጋጅቷል።
######

በሴቶች ብቻ የተመራው እና ከአዲስ አበባ ዋሽንግተን ዲሲ ያቀናው የበረራ ቡድን ዋሽንግተን ዲሲ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
######

በኮሮና(COVID 19) ስጋት መንፈሳዊ ጉዞን የከለከለችው ሳዑዲአረቢያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 11 መድረሱን አስታውቃለች።

በኢራን ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 194 ደርሷል።

ኩዌት በበኩሏ 64 ኳታር ደግሞ 15 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ይፋ አድርገዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *