መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 7፣2012

በኮሮና ቫይረስ የተነሳ በቻይና የፍቺ መጠን መጨመሩ ተሰማ።
በምዕራባዊ ቻይና ሲቹሃን ግዛት ባለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ ለፍቺ ከ300 በላይ ጥንዶች ጥያቄ አቅርበዋል።በኮሮና የተነሳ ከቤት ባለመውጣት በጋራ ረጅም ሰዓታት ለማሳለፍ የተገደዱ ጥንዶች ድብርት ተፈጥሮብናል ሲሉ ፍቺ ለመፈፀም አመልክተዋል።

############
############

በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 6518 ደረሰ።

በቫይረሱ በመላው አለም የተያዙ ሰዎች ቁጥር 169,605 ሲደርስ 77,776 ሰዎች አገግመው ከሆስፒታል መውጣታቸው ተሰምቷል።

###########
###########

በጀርመን ተወዳጅ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የሆነው የቢግ ብራዘር ውድድር ሲሆን ተወዳዳሪዎች እስካሁን ድረስ ስለ ኮሮና ቫይረስ የሰሙት መረጃ የለም።ውድድሩ ከቴክኖሎጂ የሚያራርቅ ሲሆን ማንም ስለ ኮሮና ቫይረስ ለተወዳዳሪዎቹ የነገራቸው የለም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *