መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 13፣2012


አጫጭር የዛሬ መረጃዎች
~ ሲንጋፖር ለአጭር ለአጭር ጊዜ ጉብኝት ወደ ሀገሪቱ ዜጎች እንዳይመጡ ከለከለች።
~ በኢንዶኔዥያ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የ48 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 514 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
~ ታይዋን የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል እንዲቻል የትራንዚት መንገደኞች ከማክሰኞ መጋቢት 15 ጀምሮ ከለከለች።
~ በኢኳዶር በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ400 መብለጡ ተሰማ።
~ የአውስትራልያ ታላላቅ ከተሞች ሜልቦርብ እና ሲድኒ ለቀጣዮቹ 48 ሰዓታት ከእንቅስቃሴ የተገደቡ መሆኑ ተገለፀ።
~ በፍልስጤም ጋዛ ሰርጥ ሁለት ግለሰቦች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
~ በአርጀንቲና በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 158 ደርሷል።
~ ጃማይካ ወደ ኢራን፣ቻይና፣ደቡብ ኮርያ፣ጣሊያን፣ሲንጋፖር፣ጀርመን፣ስፔን፣ፈረንሳይ እና እንግሊዝ የጉዞ ክልከላን አወጀች።
############################
ኢራን የአሜሪካን ላግዝሽ ማለት ውድቅ አደረገች
የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኬሆማኒ የኮሮናን ስርጭት ለመከላከል በአሜሪካ የቀረበውን እናግዛችሁ ጥሪ አንቀበልም፤የአሜሪካ መሪዎች ውሸታም ናቸው ብለዋል።በኢራን በኮሮና የተነሳ የ1,556 ሰዎች ህይወት አልፏል።
############################
አውስትራሊያ ከነገ መጋቢት 14 ጀምሮ የምሽት መዝናኛ ቤቶች፣የቁማር ቤቶች፣ሲኒማ፣የአምልኮ ስፍራዎች እንዲዘጉ ውሳኔ አሳለፈች።ጠ/ሚ ሞሪሰን ካቢኔያቸውን ሰብስበው እንዳስታወቁት የቤት ለቤት የሸቀጣ ሸቀጥ አቅርቦት ይቀጥላል ብለዋል።
############################
የራሺያ ጦር ለጣልያን የህክምና ድጋፍ ለማድረግ በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ውሳኔ መሰረት በዛሬው እለት ያቀናሉ።በራሺያ 306 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *