መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 14፣2012

እውቁ አሜሪካዊ ፕሮዲውሰር ሀርቪ ዊኒስቴን በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል።

ግለሰቡ በቅርቡ በወሲብ ቅሌት ተፈርዶበት ወደ ማረሚያ ቤት ያቀና ሲሆን በኒውዮርክ ማረሚያ ቤት በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

############
############

ግብፅ መከላከያ ዋና ጄነራል ካሊዲ ሻልታዉት በኮሮና_ቫይረስ የተነሳ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ፡፡

በግብፅ 294 ሰዎች በኮሮና ቫይርስ የተያዙ ሲሆን የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን አህራም ኦን ላይን ዘግቦታል፡፡

############
############

ሶሪያ በትናንትናው እለት የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ በሀገሯ ማግኘቷን ሪፖርት አድርጋለች

እ.ኤ.አ ከ 2011ዱ ከፀደዩ የአረብ አብዮት አንስቶ መረጋጋት የተሳናት ሶሪያ የኮሮና ቫይረስ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮባታል፡፡

የሶሪያ የጤና ሚኒስትር አል ያዚጂ እንደተናገሩት የ 20 ዓመት እድሜ ያላት ግለሰብ በኮሮና ቫረስ መያዟ ይፋ ተደርጓል፡፡

የሶሪያ ጎረቤቶች በቫይረሱ ክፉኛ መጎዳታቸው ይታወቃል፡፡

በደማስቆ በትላንትናው እለት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ መንግስት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡ ት/ቤቶች ፣ሬስቶራንቶችና የህዝብ መገልገያዎች ተዘግተዋል፡፡

የሶሪያ መንግስት ደጋፊ የሆነችው ኢራን በቫይረሱ ክፉኛ ተጎጂ የሆነች ሲሆን ከኢራን ሳይዛመት እንዳልቀረ ተነግሯል፡፡

############
############

አጫጭር መረጃዎች

~ በህንድ በእረፍት ቀናቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ጨምሮ 359 ደረሰ።የህንድ መዲና ኒው ዴሊህ የ18 ሚሊየን ህዝቦች መኖሪያ ስትሆን በከተማዋ 29 ሰዎች መያዛቸው ተረጋግጧል።

~ የካናዳ ብሄራዊ የኦሎምፒክ ቡድን ከቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ራሱን አግሏል።

~ በስሪላንካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 77 ደርሷል።

~ በፊሊፒንስ በ24 ሰዓት ውስጥ 8 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አለፈ።በአጠቃላይ የሟቾቹ ቁጥር 33 ሲደርስ 396 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

~ በታይላንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 721 ደረሰ ከነዚህ መካከል 52 ሰዎች ማገገማቸው ተሰምቷል።

~ በፓናማ በ24 ሰዓት ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 28 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 313 ደርሷል።

############
############

ትራምፕ በድጋሚ የኮሮና ቫይረስን “የቻይና ቫይረስ” ሲሉ ጠሩ።

አሜሪካዊው ፖለቲከኛ የኬንታኪ ሴናተር ራንድ ፖል በቫይረሱ መያዙን ተከትሎ ትራምፕ በቲውተር ገፃቸው ወዳጄ “በቻይና ቫይረስ” ተይዟል።
ይህ መልካም አይደለም እሱ ጠንካራ ሰው ነው እንዲያገግም መመኘታቸውን ቲውት አድርገዋል።የትራምፕን የቲውተር
መልዕክት ተከትሎ ቤጂንግ ቁጣዋን ገልፃለች።

############
############

በኮሎምቢያ መዲና ቦጎታ በተቀሰቀሰ አመፅ የ 23 ታራሚዎች ህይወት ሲያልፍ 83 ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል፡፡

የኮሎምቢያ የፍትህ ሚኒስቴር ለግጭቱ መነሻ የሆነው በዓለም ዙሪያ የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስን ተከትሎ ፤ የቦጎታ ማረሚያ ቤቶች ተገቢውን ንፅህና የጠበቀ አይደለም ሲሉ ጥያቄ ማንሳታቸውን ገልጿል፡፡

በኮሎምቢያ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ 231 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን የሁለት ሰዎች ህልፈተ ህይወት ተሰምቷል፡፡

የኮሎምቢያ የፍትህ ሚኒስትሯ ማርጋሬታ ካቤሎ አመፁ የተነሳው ከማረሚያ ቤቶች ሰዎች ለማምለጥ ያደረጉት ጥረት ነው ስትል ተናግራለች፡፡

በኮሎምቢያ 81ሺህ ታራሚዎችን እንዲይዙ በተገነቡ ማረሚያ ቤቶች ከ 121ሺህ በላይ ታራሚዎች በተጨናነቀ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *