መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 15 ፣ 2012

በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት ሰዎች 102,429 ሰዎች ማገገማቸው ተሰማ።በመላው አለም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 381,761 ሲደርስ 16,558 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

##############
##############

ቱርክ በኮሮና_ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 37 ደርሷል።ይህንኑ ተከትሎ የአንካራ መንግስት የጉዞ ክልከላ እና የሱቆች የመክፈቻና የመዝጊያ ሰዓታት ገደብ ተቀምጧል።በቫይረሱ 1,529 ሰዎች ተይዘዋል።

##############
##############

አጫጭር መረጃ ከአፍሪካ

~ በሩዋንዳ የኮሮና ስርጭት በእጥፍ ጨመረ።በ17 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን ተከትሎ በአጠቃላይ ኮሮና የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 36 ደርሷል።

~ በሩዋንዳ በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች መካከል አንዱ ብቻ ከሀገር ውስጥ መያዙ ሲረጋገጥ ቀሪዎቹ ከኢምሬቶች፣ኬንያ፣አሜሪካ፣ህንድና ኳታር የመጡ ግለሰቦች ላይ ተገኝቷል።

~ በጋና በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ሁለተኛ ሞት ተመዘገበ።27 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

~ ሴኔጋልና አይቮሪኮስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመገደብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አውጀዋል።በእንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጥሏል።

~ በዩጋንዳ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ስምንት ሰዎች የተለዩ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9 ደርሷል።ሁሉም ግለሰቦች ወደ ዱባይ አቅንተወ እንደነበረም ተረጋግጧል።

~ በናይጄሪያ 4 ተጨማሪ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተገኙ ሲሆን አንዱ በመዲናዋ አቡጃ ሶስቱ ደግሞ በሌጎስ ናቸው።በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 40 ደርሷል።

##############
##############

አጫጭር መረጃዎች

~ በካምቦዲያ በኮሮና ቫይረስ ዙርያ መረጃ አጋርተዋል በሚል ከወርሃ ጥር መጨርሻ አንስቶ 17 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን ተችተዋል።

~ በጀርመን በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 4,764 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በሀገሪቱ 29,056 ሲደርስ የ123 ሰዎች ህይወት አልፏል።

~ የደቡብ ኮርያ መንግስት በኮሮና ክፉኛ የተጎዳውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚና የአክስዮን ገበያ መቀዛቀዝ እንዲያገግም የ100 ትሪሊዮን ዋን ወይም 80 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማዕቀፍ አዘጋጀ።

~ ማይናማር በሀገሯ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ሪፖርት አደረገች።ከእንግሊዝና አሜሪካ የመጡ ሁለት ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

~ በኒውዝላንድ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 40 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 155 ደርሷል።

~ በታይላንድ በ24 ሰዓት ውስጥ የ106 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12 ደረሰ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *