መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 18፤2012- ብስራት የምሽት አጫጭር ወሬዎች

አጫጭር መረጃዎች
~ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የስልክ ውይይት ከእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ጋር አድርገዋል።ከዋይት ሀውስ በወጣ መረጃ በቶሎ እንዲያገግሙ ትራምፕ ለቦሪስ ጆንሰን መመኘታቸው ተገልጿል።
~ የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ይፋ ባደረገው መረጃ በላቲን አሜሪካና በካሪቢያን ሀገራት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ10ሺ በላይ ሆኗል።
~ የዙምባብዌ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ እንዳስታወቁት ከሰኞ መጋቢት 21 ጀምሮ በሀገሪቱ ለሶስት ሳምንት ያህል እንቅስቃሴ እንደሚገደብ ይፋ አደረጉ።
~ በደቡብ አሜሪካ ከሚገኙ ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ የተጎዳችዉ ብራዚል የ77 ዜጎቿን ህይወት ስትነጠቅ 3,027 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
~ ቤልጄየም ከቤት ያለመውጣት መመሪያን በሁለት ሳምንት በማራዘም እንቅስቃሴ የገደበች ሲሆን ተመሳሳዩን የማራዘም እርምጃ ፈረንሳይ እንደምትወስድ ይጠበቃል።
~ የህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ለእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት ብርቱ ነህና ታሸንፋለህ ሲሉ አጋርነታቸውን ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *