መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 23፤2012- ብስራት የማለዳ አጫጭር መረጃዎች

አጫጭር መረጃዎች
~ በእንግሊዝ ኪንግስ ኮሌጅ በተሰራ ጥናት የማሽተት እና የመቅመስ ስሜትን ማጣት የኮሮና ቫይረስ ምልክት እንደሆነ ይፋ ተደረገ።በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች 59 በመቶ ያህሉ ላይ ይህንነ ማስተዋል መቻሉን ጥናቱ አመላክቷል።
~ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያጋጠመውን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብልን በተመለከተ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ስካርፍ ተጠቀሙ ሲሉ ምላሽ ሰጡ።በአሜሪካ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 4,055 ደርሷል።
~ በቦትስዋና የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ሞት ሪፖርት ተደረገ።ወደ ደቡብ አፍሪካ ተጉዘው የነበሩ የ79 አመት አዛውንት ህይወታቸው ማለፉ ተገልፆል።
~ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከወባ፣ኩፍኝ፣ኮሌራ፣ኢቦላና ኮሮና ጋር እየታገለች መሆኑን ይበልጥ ደግሞ ህፃናት ተጎጂ ስለመሆናቸው ዩኒሴፍ አስታወቀ።
~ በኔዘርላንድ ለቀጣዮቹ 28 ቀናት ትምህርት ቤቶች፣ምግብና መጠጥ ቤቶች ተዘግተው እንደሚቆዩ ጠቅላይ ሚንስትር ማርክ ሩቲ አስታወቁ።
~ በአውስትራልያ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ 60 ያህል የህትመት ጋዜጦች ህትመት እንዳቆሙ የአውስትራልያ ሚዲያ ግሩፕ ዋና ሀላፊ ሚካኤል ሚለር ተናገሩ።
~ በካናዳ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 101 ሲደርስ 9,887 ሰዎች በቫይረሱ ስለመያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።
~ በሜክሲኮ ሰሜናሜ ግዛት በሚገኝ ሆስፒታል 29 ዶክተሮች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተሰማ።እስካሁን በሀገሪቱ 1,215 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የ29 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *