አጫጭር መረጃዎች
~ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከቤት መውጣትን የከለከለችው ቱኒዚያ በመዲናዋ ቱኒስ የሮቦት ፖሊስ ወደ ስራ አስገባች።ሮቦቱ የዜጎችን እንቅስቃሴ ይከታተላል።በቱኒዚያ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 14 ደርሷል።
~ የኢራን ግዙፉ አየርመንገድ ኤር ኢራን በኮሮና ቫይረስ ስጋት በጀርመን የሚያደርገውን በረራ በሙሉ ሰረዘ።
~ በደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የወጣውን ህግ የተላለፉ ከ17ሺ በላይ ዜጎች በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ መታሰራቸው ተሰማ።በደቡብ አፍሪካ 1,500 የሚጠጉ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
~ አርጀንቲና በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ወደ አውሮጳ ሀገራት ትልከው የነበረው የበሬ ስጋ ግብይት በመቀዛቀዙ ክፉኛ መጎዳቷ ተገለፀ።
~ እንደ ፔሩ ሁሉ ፖናማም ለግብይት ከቤት መውጣት የሚቻለው በጾታ ነው ስትል አስታወቀች።ሰኞ፣እሮብና አርብ ለወንዶች ማክሰኛ፣ሀሙስ እና ቅዳሜ ገበያ መሄድ የሚችሉት ሴቶች ብቻ ናቸው።አስቀድማ ከፓናማ ፔሩ ይህንን ህግ አውጥታለች።
~ የሜክሲኮ ፕሬዝዳንት አንድሬስ ማኑኤል ኦብራዶር በኮሮና ጊዜ በወንጀለኛ ቡድኖች የሚፈፀሙ ወንጀሎች በሜክሲኮ ስጋት እየፈጠሩ መሆኑን አስታወቁ።
~ በካናዳ በኮሮና ቫይረስ የተነሣ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 173 ሲደርስ የተጠቂዎች ቁጥር 11,747 መድረሱን የካናዳ መንግስት አስታውቋል።