መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 2፣ 2012 ዓ.ም

አጫጭር መረጃዎች

~ የብራዚል ፕሬዝዳንት ቦልሴናሮ የአካላዊ ፈቀቅታን መመሪያ በመጣስ በብራዚላ ከተማ ጎዳናዎች እንቅስቃሴ በማድረግ ለተከታዮቻቸው ሰላምታን እየሰጡ ማለፋቸው ትችትን አስከትሏል።ብራዚላውያኑ ፕሬዝዳንቱ ለኮሮና እየሰጡት ያለው የተዘናጋ ምላሽ አስቆጥቷቸዋል።

~ በሊቢያ ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን ህክምና ሱሰጥ የነበረው ሆስፒታል ለሶስት ጊዜ ያህል በተሰነዘረበት ጥቃት አገልግሎት መስጠት አቆመ።የትሪፖሊ መንግስት ለጥቃቱ ተጠያቂው የሀፍታር ሀይሎች ናቸው ብሏል።

~ በቱርክ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ብቻበኮሮና ቫይረስ የ98 ሰዎች ህይወት አልፏል። ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 1,006 ሲደርስ 47,029 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

~ ፖርቹጋል የጉዞ ክልከላ ህጉን ለቀጣዮቹ 21 ቀናት አራዘመች።አየርላንድ በተመሳሳይ ለ24 ለተጨማሪ 25 ቀናት የጉዞ ክልከላ ህጉን አራዝማለች።

~ ኢራን በእስራኤል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ 5800 ፍልስጤማውያን በኮሮና ቫይረስ ሊያዙ ይችላሉ ስትል ስጋቷን ገለፀች።

~ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ኔቶ መራሹ የኮሶቮ ልዑክ አባል በኮሮና ቫይረስ መያዙ ሪፖርት ተደረገ።በኔቶ የኮሶቮ ልዑክ 3,500 ወታደሮች ይገኛሉ።

~ በናይጄሪያ ሌጎስ ግዛት የጤና ኮሚሽነር ቤት ለቤት ለሚመጡ የጤና ባለሙያዎች የሌጎስ ግዛት ነዋሪዎች እንዲተባበሩ ጥሪ ቀረበ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *