መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 3፣ 2012 ዓ.ም

አጫጭር መረጃዎች

~ የእንግሊዝ መንግስት በዙምባብዌ የሚገኙ ዜጎቹን ከኮሮና መስፋፋት ጋር በተያያዘ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ትዕዛዝ አስተላለፈ።የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ዋና ፀሀፊ ዶምኒክ ራአብ በተለያዩ ሀገራት ያሉ የእንግሊዝ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል ።

~ የጃፓን ሶፍት ባንክ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወንድ ልጅ ከቀጣዩ ወር ጀምሮ በየወሩ 300 ሚሊየን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለሽያጭ እንደሚያቀርብ አስታወቁ።ለዚህም ከቻይናው ቢዋይዲ የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ ጋር ውል አስሯል።ቢዋይዲ የተሽከርካሪ ሽያጭ በመቀዛቀዙ ማስክ በማምረት ላይ ይገኛል።

~ በካዛኪስታን ግዙፉ የነዳጅ ማጣሪያ ስፍራ ቴንጊዝ የኮሮና ቫይረስ መዛመቱ ተሰማ።በማጣሪያው ካምፕ ውስጥ ካሉ ሰራተኞች 12ቱ በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።በቼቭሮን ኩባንያ የሚመራ የነዳጅ ማጣሪያ ሲሆን ኩባንያ በማዕከላዊ እስያ ቁጥር አንድ የነዳጅ አቅራቢ ነው።

~ በኔዘርላንድ ባለፉት 24 ሰዓታት 1,316 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 24,413 ደርሷል።ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 2,643 መድረሱ ሪፖርት ተደርጓል።

~ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ ከሀገር ውጪ ያሉ ጃፓናውያን በምሽት ሰዓታት ወደ መጠጥ ቤቶች ከመሄድ እንዲቆጠቡ ጥሪ አቀረቡ።

~ በማሌዥያ ባለፉት 24 ሰዓታት 184 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሪፖርት ተደረገ።በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4,530 ሲደርስ 77 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።ከህሙማኑ መካከል 44 በመቶ ማገገማቸውን የማሌዥያ የጤና ሚንስቴር አስታውቋል።

~ የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትሯ ፓቴል ለህክምና ባለሙያዎች በቂ የመከላከያ ቁሳቁስ ባለማቅረባችን ይቅርታ እንጠይቃለን ስትል ተናገረች።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *