መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 6፣ 2012 ዓ.ም

አጫጭር መረጃዎች

~ የዙምባብዌ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ለ21 ቀናት የታወጀ የእንቅስቃሴ ገደብ ተራዘመ የሚል የሀሰት ዜናን ያሰራጨው ሰው ማንነቱ ሲደረስበት የ20 ዓመታት እስር ይጠብቀዋል አሉ።መማሪያ ይሆናል የሀሰት ዜናን አንፈልግም ብለዋል።በቫይረሱ ዙርያ የውሸት ዜና የሚያሰራጩ ሰዎችን ዙምባብዌ በ20 ዓመት እስር እንደምትቀጣ አስቀድማ አሳውቃ ነበር።

~ በኒው ዮርክ ባለፉት 24 ሰዓት የተመዘገበው የሞት መጠን ከሰኞ አንፃር ጨምሯል።778 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ሲደረግ ሰኞ እለት የሟቾች ቁጥር 671 ነበር።የኒው ዮርክ ገዢ ኩሞ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 1600 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተናግረዋል።

~ በሩሲያ በዛሬው እለት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው በኮሮና ቫይረስ የተጠቃበት ሆኖ ተመዝገቧል።2774 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲነገር ከ50 በመቶ በላይ በመዲናዋ ሞስኮ ነው።

~ በሞንቴኔግሮ እሁድ የሚከበረው የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች የትንሳኤ በዓል በቤተክርስቲያን መሰብሰብ ተከልክሏል።

~ በቱርክ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 107 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል።በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 1,403 ደርሷል።65,111 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል 4,799 ያህሉ አገግመዋል።በቱርክ በየእለቱ ከ30ሺ በላይ ሰዎች ላይ ምርመራ ይደረጋል።

~ ፖላንድ ከፊታችን እሁድ አንስቶ ቀስ በቀስ እንቅስቃሴ የሚገድበውን ህግ እንደምታነሳ አሳወቀች።በሀገሪቱ በግንቦት 2 ብሄራዊ ምርጫ እንደሚደረግ ይጠበቃል።

~ ብራዚል አነስተኛ ምርመራ እያደረገች በመሆኑ እንጂ በኮሮና ቫይረስ የተያዘው ህዝብ ብዛት ከተነገረው በ12 እጥፍ ሊበልጥ እንደሚችል አንድ ጥናት መጠቆሙን ሮይተርስ ዘግቧል።

~ በታይዋን ከወር በኃላ ለመጀመሪያ ግዜ የኮሮና ቫይረስ አዲስ ኬዝ ያልተመዘገበበት ቀን የዛሬው እለት ሆኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *