መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 7፣ 2012 ዓ.ም ብስራት ማለዳ አጫጭር መረጃዎች

አጫጭር መረጃዎች

~ ማላዊ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የ21 ቀናት የእንቅስቃሴ ገደብን አደረገች።በማላዊ 16 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ሲደረግ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

~ የአውሮጳ ህብረት የ50 ሚሊዮን ድጋፍ ለናይጄሪያ ማድረጉ ተሰማ።ድጋፉ ናይጄሪያ ቫይረሱን ለመግታት ለምታደርገው ጥረት የሚያግዝ ይሆናል።

~ በዴንማርክ በዛሬው እለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይከፈታሉ።በዴንማርክ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ይገኛል።ከ6,700 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 300 የሚሆኑ ሰዎች ህይወት አልፏል።

~ ታይላንድ የአየር በረራ ለቀጣዮቹ 16 ቀናት እንዳይደረግ ክልከላ አድርጋለች።የአየር በረራ ክልከላው ሲራዘም የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።በሀገሪቱ በቫይረሱ የ41 ሰዎች ህይወት አልፏል።

~ በመላው አለም በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ126ሺ በላይ ሆኗል።ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበባቸው ሀገራት አሜሪካ፣ጣልያን፣ስፔን፣ፈረንሳይና እንግሊዝ ናቸው።

~ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በመላው አለም የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርጎ ኮሮና ላይ ብቻ ትኩረት እምዲደረግ ከፀጥታው ምክር ቤት አምስት አባል ሀገራት ሶስቱ ድጋፍ መስጠታቸውን አሳወቁ።

~ ፓኪስታን ለሁለት ሳምንታት ያህል የእንቅስቃሴ እገዳን አራዘመች።በሀገሪቱ የሚገኙ ግዙፉ ኢንዱስትሪዎች ቀስ በቀስ ወደ ስራ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

~ በቬትናም የሀሰት ዜናን የሚያሰራጩ ሰዎች ከ426 አሜሪካን ዶላር እስከ 853 የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስቀጣ መንግስት አሳሰበ።የቅጣት ገንዘቡ መጠን አማካይ የቬትናም ሰራተኞች ከ3 እስከ 6 ወራት ደሞዝ ይደርሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *