መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 7፣ 2012 ዓ.ም

ባለፋት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 431 የላብራቶሪ ምርመራ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚንስትር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 85 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-

~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ431 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ በሶስት ግለሰቦት ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡

~ ሶስቱ ግለሰቦች ኢትዮጲያዉያን ናቸው፡፡

~ ታማሚ ቁጥር 1 ኢትዮጰያዊ ወንድ እድሜ 43 ከአሜሪካ የመጣ እና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረ

~ታማሚ ቁጥር 2 ኢትዮጰያው ወንድ እድሜ 30 ከበሽታዉ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው

~ታማሚ ቁጥር 3 ኢትዮጰያው ወንድ እድሜ 24 ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው

ተጨማሪ መረጃ
~ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 4,988 ደርሷል።

~ አንድ ግለሰብ ከቫይረሱ አገግመዋል

~ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች 15 ድርሰዋል

~ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 65 ናቸው።

~ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *