መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 8፣ 2012 ዓ.ም

ለትንሳኤ በዓል የመብራት መቆራረጥ እንዳይኖር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጥንቃቄ ስራዎችን እያከናወንኩ ነው አለ

በመጪው የትንሳኤ በዓል ኢንዱስትሪዎች ከግሪድ ኃይል እንዳይጠቀሙ ተጠይቋል።

ከበዓሉ በፊት የኃይል መቆራረጥ የሚበዛባቸውን መስመሮችና አካባቢዎች በመለየት ጭነት የማመጣጠንና የቅድመ መከላከል ጥገና ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያቶች ለሚፈጠሩ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ አስቸኳይ ጥገና ለመስራት ዝግጅትም ተደርጓል ተብሏል፡፡

ሆኖም ከዓቅም በላይ በሆነ ችግር በኤሌክትሪክ መስመሩ ላይ ከፍተኛ የኃይል መጨናነቅ ሊከሰት ስለሚችል፤ የድንጋይ ወፍጮ፣ የፕላስቲክ፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የብረታ ብረት፣ የቆዳና ቆዳ ዉጤቶች፣ የኬሚካልና ሌሎች የከፍተኛና የመካከለኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች በበዓሉ ዋዜማ ከዋናው የኃይል ቋት /ግሪድ/ ኤሌክትሪክ እንዳይጠቀሙ ተቋሙ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምንጭ፡-ብስራት ራዲዮ (ሚኪያስ ፀጋዬ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *