መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 8፣ 2012 ዓ.ም

ስጋ መብላት ተከልክሏል እየተባለ በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የሚናፈሰው ወሬ ተራና መሰረት ቢስ ሀሳብ ነው ፡ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰዒድ እንድሪስ

የጤና ባለሙያዎች ጥሬ ስጋ እንዳይበላ የሚል ክልከላን እንዲሁም መንግስት በአዋጁ በተካተተው መሰረት በግዢ ወቅት የሚፈጠር አካላዊ ጥግግትን እንዳይኖር ከልክሏል እንጂ ስጋ መብላት ተከለከለ እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ የሀሰት ስለመሆኑ አቶ ሰዒድ ተናግረዋል።

አክለውም በተለይም ህብረተሰቡ ኢ-መደበኛ ግዢ በሚፈፀምበት ወቅት በባህላዊ መንገድ ፤ በገዥና በሻጭ መካከል ያለው የእጅ መሳሳም እንዲቀርና ወደ ጅርጅቱ እንስሳቱን በመውሰድ በተገቢው ሁኔታ እንዲያሳርድ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

(ሚኪያስ ፀጋዬ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *