መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 8፣ 2012 ዓ.ም

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን የፋሲካ በዓልን አስመልክቶ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችን ቦታው ድረስ በመገኘት አበረታተዋል።

በኤካ ኮተቤ ሆስፒተሰል የተገኙት መሪዎቹ በተቋሙ እያገለገሉ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎችም የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክተዋል።

የአረጋውያንን ቤት ማደስ መርሀግብር ሲጀመር ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድና ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በመገኘት መርሀግብሩን ያስጀመሩበት እማሆይ አዱኛ መኖሪያ ቤትና የአካባቢው ነዋሪዎች መኖሪያ ቤት በመገኘትም ለፋሲካ በዓል የሚሆኑ የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክተዋል።

በተጨማሪም አፍንጮ በር አካባቢ ሚገኝ የህፃናት ማሳደጊያ ተገኝተው የፋሲካ በዓል ስጦታ አበርክተዋል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ጠ/ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ህብረተሰቡ እርስ በእርሱ እንዲረዳዳ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ህብረተሰቡ በየአካባቢው ድጋፍ የሚያደርግበት 1200 የምግብ ባንኮች አቋቁሟል።

Via ከንቲባ ጽህፈት ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *