ጦማር/ዜና

ሚያዝያ 14፣ 2012-በቋራ ወረዳ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ተያዘ

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውር የተገኘ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ገለፀ ፡፡

የቋራ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ተወካይ ኃላፊ ዋና ሳጅን ዳምጠው ሞላ ለኢዜአ እንደተናገሩት ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው ሚያዚያ 12 ቀን 2012 ዓም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ በወረዳው ነብስ ገበያ ቁጥር አንድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተለያዩ ጥይቶችን ይዞ ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ነው ።

ግለሰቡ የሰሌዳ ቁጥር በሌለው ሞተር ሳይክል ሲንቀሳቀስ 1 ሺህ 142 የክላሽኮቭና 500 የብሬን ጥይቶች እንዲሁም 38 የክላሽን ካዝናዎች ይዞ መገኘቱን ገልፀዋል።

ወረዳው ከሱዳን ጋር የሚዋሰን በመሆኑ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል በወጣው አዋጅ መሰረት የፀጥታ አካላት ቁጥጥር በሚያደርጉበት ወቅት ግለሰቡ እንደተያዘም ዋና ሳጅኑ ተናግረዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *