መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 17፣2012-አጫጭር መረጃዎች

~ በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ አርቲስቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን በማስዋብ ጭምር ዜጎች እንዲጠቀሙ እያበረታቱ ይገኛል፡፡በጋዛ 17 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ሪፖርት ተደርጓል፡፡

~ በደቡብ አፍሪካ በአንድ የመድሃኒት ፋብሪካ ዉስጥ ከሚሰሩ ሰዎች 99 የሚሆኑት ላይ በላብራቶሪ በተደረገ ምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸዉ፡፡

~ ሲሪላንካ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለአምስት ሳምንታት ተጥሎ የቆየዉን ከቤት ያለመዉጣት ህግ ከሰኞ ጀምሮ እንደምታነሳ አስታወቀች፡፡ሆኖም ግን በመዲናዋ ኮሎምቦ እና በ4 የወደብና የባህር ዳርቻ ስፍራዎች ክልከላዉ ይቀጥላል፡፡

~ በኢራን በየእለቱ የሚመዘገበዉ የሞት መጠን ከፍተኛ ከነበረበት ቀናቶች አንጻር 70 በመቶ መቀነሱ ተሰማ፡፡ባለፉት 24 ሰዓት በኮሮና ቫይረስ የ76 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 5,650 ደርሷል፡፡

~ በህንድ እና ፓኪስታን አንዳንድ ክልከላዎች መነሳት ጀምረዋል፡፡በዛሬዉ እለት በህንድ ከአንድ ወር በኃላ በመኖሪያ ቤት አካባቢ የሚገኙ ሱቆች ተከፍተዋል፡፡በፓኪስታን በጥብቅ የደህንነት ማስጠንቀቂያ ሱቆች እንዲከፈቱ ተደርጓል፡፡

~ የአለም አቀፉ የእግርኳስ ፌደሬሽን ፊፋ ለአባል ሀገራቱ የኮሮና ቀዉስ ያደረሰዉን የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ የ150 ሚሊየን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ለአባል ሀገራቱ ድጋፍ ይደረጋል፡፡ፊፋ 211 አባል ሀገራት አሉት፡፡

~ ሰርቢያ ለጣልያን የጤና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች፡፡እ.ኤ.አ በ2014 ሰርቢያ ከባድ የጎርፍ አደጋ ባጋጠማት ወቅት ጣልያን ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጓ ይታወሳል፡፡ይህንን እርዳታ ለማመስገን ትክክለኛዉ ጊዜ አሁን ነዉ ሲል የሰርቢያ መንግስተ ተናግሯል፡፡የጣሊያኑ ፊያት መኪና በሰርቢያ ከ20 ሺ በላይ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *