መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 19፣2012-በኢትዮጵያ በቢጫ ወባ በሽታ 86 ሰዎች መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አነሞር እና ኤነር ወረዳ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ የበሽታው ምልክት መታየቱን ሪፖርት መደረጉን ገልፀዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ከክልሉ ጤና ቢሮ እና ከዞኑ ጤና መምሪያ ጋር በመሆን የምላሽ አሰጣጡን ሲደግፍ እንደነበርም ተናግረዋል።

በመሆኑም የካቲት 24 ቀን 2012 ዓ.ም በሽታው እንደጀመረ ያስታወቁ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በበሽታው የተያዘ ሰው ሪፖርት የተደረገው መጋቢት 20 ቀን እንደሆነ አስታውቀዋል።

በዚህም እስካሁን 86 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው እና አራት ሰዎችም ህይወታቸው ማለፉን ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

በወረዳው በሽታው በስፋት በታየባቸው አምስት ቀበሌዎች የቤት ለቤት ቅኝት የተካሄደ ሲሆን በዚህም 1 ሺህ 225 ቤቶች እና ሁለት ትምህርት ቤቶች በቅኝቱ ታይተዋል ነው የተባለው።

እንዲሁም ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው የተባሉ 27 ሺህ 178 ሰዎች የቢጫ ወባ ክትባት መከተባቸውን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

ወረርሽኙንም መጋቢት 20 ቀን ላይ መቆጣጠር መቻሉ የተገለፀ ሲሆን ከዚያን ጊዜ በኋላ አዲስ ታማሚ ሪፖርት አልተደረገም ነው ያሉት።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *