
~ በብሩንዲ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣዩ ወር ለሚካሄደዉ ሀገር አቀፍ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ ጀመሩ፡፡የ11 ሚሊየን ህዝቦች መኖሪያ በሆነችዉ ብሩንዲ ምርጫዉ ሰብዓዊ ቀዉስ እና አለመረጋጋት እንደሚፈጥር ከወዲሁ ተሰግቷል፡፡አንድ ሰዉ በኮሮና ቫይረስ በብሩንዲ ህይወቱ ሲያልፍ 15 ሰዎች ተጠቅተዋል፡፡
~ ዩጋንዳ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ለ833 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገች፡፡በይቅርታዉ የሚያጠቡ እናቶች፣አዛዉንቶች፣ነፍሰ ጡር ታራሚዎች ቅድሚያ አግኝተዋል፡፡በዩጋንዳ ከ63ሺ ያላነሱ ታራሚዎች አሉ፡፡
~ የላይቤሪያ የፍትህ ሚንስትር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸዉ ተነገረ፡፡ሚንስትሩ ፍራንክ ሙሳ ዲን ከመዲናዋ ሞኖሮቪያ ዉጪ ባለ የጤና ተቋም የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛል፡፡
~ የዩናይትድ ኪንግደም የፍትህ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀዉ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የ15 ታራሚዎች ህይወት ሲያልፍ 5 የማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች በኮሮና ህይወታቸዉን ተነጥቀዋል፡፡
~ የኢንዶኔዥያ መንግስት ዜጎች ወደ መደበኛ ህይወት በወርሃ ሀምሌ ይመለሳሉ ሲል አስታወቀ፡፡በህዝብ ብዛቷ በአለም በአራተኛ ደረጃ የምትገኘዉ ኢንዶኔዥያ 9,096 ዜጎቿ በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡የ765 ሰዎች ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል፡፡
~ በስዊዘርላድ ጸጉር ቤቶች እና አረንጋዴ ስፍራዎች ክፍት ተደርገዋል፡፡ትምህርት ቤቶች ከ15 ቀናት በኃላ እንደሚከፈቱ መንግስት አሳዉቋል፡፡በስዊዘርላንድ 1‚640 ሰዎች ህይታቸዉን በኮሮና ቫይረስ የተነሳ አጥተዋል፡፡
~ የኒዉ ዮርክ ከተማ 64 ኪ.ሜ የሚያህል ጎዳና ለእግረኞች በቅርቡ ክፍት ይደረጋል ተባለ፡፡የከተማዋ ከንቲባ ቢል ደላስዮስ በአዉራ ገዳናዎች ላይ አስቀድመን ትኩረት እንደርጋለን ብለዋል፡፡