መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 19፣2012-ግምታዊ ዋጋቸው ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ባለፉት ስድስት ቀናት ውስጥ ከ40 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ ኬላ ጣቢያዎች ላይ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ከተያዙት የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ ጥራቱ ያልተረጋገጠ ምግብና የምግብ ነክ እቃዎች ፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ፣ ቅሽር ቡና ፣ በሀሰተኛ ሠነድና በቱሪስት ስም የገቡ ተሽከርካሪዎች ፣ ልባሽና አዳዲስ አልባሳት ፣ ሽቶ ፣ ሲጋራ ፣ የተለያዩ ዓይነቶች የጦር መሣሪያዎችና ጥይቶች እንዲሁም በገቢ ዕቃ አወጣጥ ታክስ ሳይከፈል ሊጭበረበር የነበሩ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዟል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የተያዙባቸው ቦታዎች ደግሞ ድሬደዋ ፣ ሞያሌ ፣ ሀዋሳ ፣ ባህር ዳር ፣ ሞጆ ፣ አዲስ አበባ ፣ አዋሽ ፣ ጅማ እና ሌሎች የጉምሩክ ኬላ ጣቢያዎች የተወሰኑት ናቸው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *