መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 19፣2012-116 ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 4 በተለምዶ ሰሜን መዘጋጃ እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ ፤ ከህዝብ የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 116 ሰዎች ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ሚያዝያ 18 እና 19 ቀን 2012 ዓ/ም በተለያዩ ሰዓታት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ልዩ ቦታው በአካባቢው ከሚገኙት ራሄል ሆቴል ውስጥ 35 ሰዎች እንዲሁም ቲሊሊ በሚባል ሆቴል ውስጥ 81 ግለሰቦችን ተሰብስበው ሺሻ ሲያጨሱ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ሃላፊ ኮማንደር ጃፋር ኸሊል ገልፀዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ጉዳቱን ለመቀነስ በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተከለከሉ ተግባራት ውስጥ በማንኛውም ቦታ የሺሻ ማስጨስና ጫት ማስቃም አገልግሎት መስጠት መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች ክልከላዎቹ ሲጣሱ ይስተዋላል፡፡

በተመሳሳይ በክ/ከተማው ወረዳ 10 ስምንት ሰዎችን በአንድ አነስተኛ ጠባብ ቤት ውስጥ ጫት ሲያስቅም የተገኘ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ሃላፊ ወ/ሮ ሠጂዳ ሙስማ ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *