
በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ 120 የሚሆኑ ግለሰቦች የሰርግ ስነ ስርዓት
አካሂደዋል
በክልሉ 4ሺህ 737 ሰርጎች ከህብረተሰቡ በተሠጠ ጥቆማ መሰረት ከደጋሾች ጋር በመወያየት ሰርጉ መቋረጡ የተገለጸ ሲሆን ፤ 120 የሚሆኑ ግለሰቦች ግን በእቢተኝነት ሰርጉን በማድረጋቸው በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ተጀምሮባቸዋል ሲሉ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዋና ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሳፍንት እሸቴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡