መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 20፣2012-በአዲስአበባ ባለቤት አልባ ውሾችን የማስወገድ ስራ መቆሙ ተገለፀ።

ውሾቹን የማስወገዱ ስራ የቆመው ውሻ የማምከኛ መድሀኒት ከውጪ መምጣት በመቆሙ ምክንያት ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶአደር ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን እንደተናገረው በበሽታ የተያዙ እና ያረጁ ውሾች ግን ምርመራ ተደርጎላቸው ይወገዳሉ።

በኮሚሽኑ የእንስሳት ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ፋሲካ በለጠ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ችግሩን ለመፍታት የውሻ ማምከኛ መድኃኒት ከደቡብ አፍሪካ የማስገባት ስራ ይሰራል።

በተጨማሪም የጎዳና ላይ ውሾችን እያበራከተ የሚገኘው የቆሻሻ አወጋገድ ላይ ክፍተት ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

በተያያዘም ኮሚሽኑ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር በታህሳስ ወር ከ12 ሺህ በላይ ውሾች እንዲከተቡ ማድረጉን ተናግሯል። ኮሚሽኑ በቀጣይ አመት 10 ሺህ ዶዝ የሚሆን ክትባት ውሾች በሚበዙባቸውና በተመረጡ ቦታዎች ላይ ለመስጠት አቅዷል።

ብስራት ራዲዮ (ሳምራዊት ስዩም)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *