
ደቡብ አፍሪካ፣ኬንያ፣ዩጋንዳና ሩዋንዳ ክልከላዎችን ሲያስፈጽሙ የሀይል እርምጃ እንደተስተዋለባቸዉ በመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ቢሮ አስታዉቋል፡፡
በደቡብ አፍሪካ ከኮሮና ቫይረስ ክልከላ ጋር በተያያዘ ከ17ሺ በላይ ዜጎች በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡በኬንያ 27 የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማት የኬንያ መንግስት የሀይል እርምጃ ከመዉሰድ እንዲቆጠብ ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡
በአፍሪካ 52 ሀገራት 32,100 የሚሆኑ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ሲነገር ከነዚህ መካከል የ1,428 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ 9,741 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸዉን የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል አስታዉቋል፡፡