
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 1080 ላቦራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 126 ደርሷል።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 – የ4 ዓመት እንግሊዛዊ ፤ የመኖሪያ ቦታ እንግሊዝ ፤ ከእንግሊዝ የተመለሰና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 2 – የ50 ዓመት እንግሊዛዊ፤ የመኖሪያ ቦታ እንግሊዝ ፤ ከእንግሊዝ የተመለሰና በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።