መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 20፣2012-አጫጭር መረጃዎች

~ በእንግዝ ወላጅ አባቱን በኮሮና ቫይረስ የተነጠቀዉ ወጣት የሀገሪቱ የጤና ዋና ጸሀፊ ማት ሀንኩን ይቅርታ ይጠይቁ ሲል ተናገረ፡፡የህክምና ባለሙያ የነበሩት የወጣቱ አባት ለባለሙያዎች በቂ የህክምና ቁሳቁስ የለም ብለዉ አስቀድመዉ ቢናገሩም ትኩረት ሳያገኙ ዶ/ር ቾድሀሪ በቫይረሱ የራሳቸዉን ህይወት አጥተዋል፡፡

~ የፈረንሳይ ጠ/ሚ ኢድዋርድ ፊሊፕ በሀገሪቱ እንቅስቃሴን የሚገድበዉ ህግ ተግባራዊ በመደረጉ 62ሺ ሰዎች ለኮሮና ቫይረስ እንዳይጋለጡ መደረጉን ተናገሩ፡፡ቀስ በቀስ እንቅስቃሴ የሚገድበዉ ህግ ከ14 ቀናት በኃላ እንደሚነሳ አስታዉቀዋል፡፡

~ በፔሩ በማረሚያ ቤት ዉስጥ በቂ ንጽህና የለንም የኮሮና ወረርሽኝን አስመልክቶ ይቅርታ ይደረግልን ሲሉ ታራሚዎች ያነሱት አመጽ የሶስት ታራሚዎችን ህይወት ነጠቀ፡፡በፔሩ 609 ታራሚዎችና የማረሚያ ቤት ሰራተኞች በቫይረሱ መጠቃታቸዉ ሲነገር የ13ቱ ህይወት አልፏል፡፡

~ በቻይና ዉሃን ከተማ በሚገኝ ላብራቶሪ ዉስጥ የኮሮና ቫይረስ ተፈጥሯል መባሉን የቻይና ብሄራዊ ባዮሴፍቲ ላብራቶሪ አስተባበለ፡፡ሆኖም ግን ቫይረሱ እንዴት ሊከሰት ቻለ በሚለዉ ዙሪያ አሁንም ምላሽ መስጠት አልተቻለም፡፡

~ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ በፖርቱጋል የተጣለዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የፊታችን እሁድ እንደሚያበቃ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ማርሴሎ ሬቤሎ ሶሳ አስታወቁ፡፡በሀገሪቱ በኮሮና የተነሳ የ948 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ በራሺያ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች በኢራን ከተጠቁት በለጠ፡፡በመላዉ ራሺያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 93,558 ሲደርስ የ867 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ ፈረንሳይ ከመስከረም ወር በፊት በዝግ ስታዲየምም ቢሆን የሚደረግ ስፖርታዊ ክንዉን አይኖርም ስትል አስታወቀች፡፡የሊግ 1 እና ሊግ 2 ዉድድሮች አይካሄዱም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *