መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 21፣2012-በቀጥታ ስርጭት ወቅት ሱሪ ሳያደርግ ዘገባዉን ያቀረበዉ ሪፖርት መነጋገሪያ ሆኗል

የኤቢሲ ኒዉስ (ABC) ሪፖርተር ዊል ሪቭ በትላንትናዉ ጉድ ሞርኒግ አሜሪካ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ ስለ ሰዉ አልባ አዉሮፕላን(ድሮን) መድሃኒቶችን እንዴት እንደሚያከፋፍሉ የሚያሳይ ጥንቅርን ከቤቱ እያቀረበ ነበር፡፡ታዲያ በዙህ ወቅት ከላይ ተስተካክሎ ሱፍ ኮትና ሸሚዝ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ከታች ሱሪ ሳያደርግ ዘገባዉን ሲያቀርብ በመላዉ ዓለም የሚገኙ የዝግጅቱ ተከታታዮች ይህንኑ መመልከት ችለዋል፡፡

ሪፖርተሩ ዊል ሪቭ የታዋቂዉ ተዋናይ ክርስቶፈር ሪቭ ልጅ ሲሆን ካሜራዉን ከወገቡ በላይ ብቻ እንዲታይ አድርጎ አለማስተካከሉ ለዚህ ሁኔታ ዳርጎታል፡፡ጋዜጠኛዉ በቲዉተር ገጹ ሁሉም ሰዉ የሚስቅበትን ጉዳይ እንዳገኘ ተስፋ አደርጋለዉ ሲል ቲዉት አድርጓል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *