
ባለፏት 24 ሰዓታት አራት ኢትዮጲያዉያን በቫይረሱ መያዛቸዉ ተረጋግጧል
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ፡-
~ ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ ለ766 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ በአራትት ግለሰቦች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፡፡
~ ታማሚ አንድ ኢትዮጲያዊት ሴት እደሜ 18 ከፑንት ላንድ የተመለሰችና በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ በለይቶ ለይቶ ማቆያ ዉስጥ የነበረች
~ ታማሚ ሁለት ኢትዮጲያዊት ሴት እድሜ 25 ከፑንት ላንድ የተመለሰችና በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ በለይቶ ለይቶ ማቆያ ዉስጥ የነበረች
~ ታማሚ ሶስት ኢትዮጲያዊት ሴት እድሜ 15 ከፑንት ላንድ የተመለሰችና በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ በለይቶ ለይቶ ማቆያ ዉስጥ የነበረች
~ ታማሚ አራት ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጉባ ኮሪቻ ወረዳ ወንድ እድሜ 23 የዉጪ ሀገር ጉዞ የሌለዉ በበሽታዉ ከተያዘ ሰዉ ጋር ንኪኪ እንዳለዉ በመጣራት ላይ ይገኛል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ፡-
~ አጠቃላይ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር 16,434 ደርሷል።
~ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ ስምንት ሰዎች አገግመዋል፡፡
~ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች 58 ደርሰዋል
~ በጽኑ ህሙማን ማከምያ ዉስጥ የሚገኝ ታማሚ የለም፡፡
~ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 67 ናቸው።
~ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።