መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 21፣2012-አሜሪካ በየእለቱ ለ 5ሚሊዮን ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ ልትጀምር ነው

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገሪቱ በቅርቡ በየእለቱ ለ 5ሚሊዮን ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ ትጀምራለች ሲሉ ተናገሩ፡፡

አሜሪካ ባለፉት ሁለት ወራት ለ 5.7 ሚሊዮን ሰዎች ምርመራ ማድረጓ ተገልዷል፡፡ ቁጥሩ ከፍተኛ ሲሆን ከ 1ሺህ ሰዎች ምርመራ የተደረገለት በአማካኝ 16ቱ ናቸው፡፡

በጣሊያን በኩል ከ 1ሺህ ሰዎች 30 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ ትራምፕ በቅርቡ 5ሚሊዮን ሰዎችን በየእለቱ የኮሮና የኮሮና ምርመራ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በየእለቱ 200ሺህ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር በቬትናም ጦርነት ህይወታቸውን ከተነጠቁት በላይ ሆኗል፡፡ የ 58‚220 አሜሪካውያንም ህልፈት ሪፖርት ተደርጓል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *