መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 21፣2012-አጫጭር መረጃዎች

~ የኒዉ ዮርክ ከተማ ከንቲባ በአንድ አይሁዳዊ የቀብር ስነስርዓት ላይ ሰዎች ሰብሰብ ብለዉ ለሽኝት መገኘታቸዉን ተቹ፡፡ከንቲባዉ ቢል ደላስዮስ ከ17 ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን ባጡባት ከተማ እንዲህ አይነት መሰባሰብ ተቀባይነት የለዉም ብለዋል፡፡

~ በሞሮኮ በሁለት ማረሚያ ቤቶች ዉስጥ በተደረገ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ 313 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸዉ ተረጋገጠ፡፡በሞሮኮ 80ሺ በላይ ታራሚዎች የሚገኙ ሲሆን ከ5‚654 በላይ የሚሆኑት በይቅርታ መፈታታቸዉ ይታወሳል፡፡

~ አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF)ለናይጄሪያ የ3.5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ፡፡ድጋፉ በኮሮና ቀዉስ ምክንያት ለተቀዛቀዘዉ የነዳጅ ገቢ መቀነስ የተነሳ ለናይጄሪያ ኢኮኖሚ የሚዉል ነዉ፡፡

~ በራሺያ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 99,399 ደረሰ፡፡ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 5,841 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸዉ ሪፖርት ተደርጓል፡፡

~ ቱርክ እስከ ግንቦት መጨረሻ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዉ እንደሚቆዩ አሳወቀች፡፡በቱርክ 115ሺ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸዉ ሲረጋገጥ ከ3ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

~ የብሪቲሽ አየር መንገድ ከዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ድጋፍ እንደሚያስፈልገዉ አስታወቀ፡፡

~ የኬንያ የህክምና ምርምር ኢንስቲትዩት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎች እንዳለቁበት አስታወቀ፡፡ቢያንስ የ7.3 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ እንደሚያሻዉ ስታር ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *