መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 21፣2012-ከሀረሪ ማረሚያ ቤት በር ገንጥለው ለማምለጥ ሞክረው የነበሩ ታራሚዎች እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ የእስራት ቅጣት ተፈረደባቸው።

ታራሚዎቹ መጋቢት 27 ቀን 2012 ዓ.ም የማረሚያ ቤቱን ዋና በር ገንጥለው ለመውጣት ሲሞክሩ በማረሚያ ቤቱ ፖሊሶች ጥረት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

በዕለቱ በማረሚያ ቤቱ ሁከት በማስነሳት ሌሎች የህግ ታራሚዎችን ለማስመለጥ የሞከሩት ተጠርጣሪዎቹ በጥበቃ ላይ በነበሩ የማረሚያ ፖሊስ አባላት ላይ ድንጋይና ሌሎች ነገሮችን መርወራቸውን የማረሚያ ቤቱ ኮሚሽነር አለምፀሀይ ታደሰ ተናግረዋል።

የብረት አልጋዎችን ከመኝታ ክፍል በማውጣት ከጥቅም ውጪ በማድረግ ጉዳት ባደረሱ 28 ታራሚዎች ላይ የሀረሪ ክልል ፖሊስ ምርመራ ሲያደርግ ቆይቷል።

የተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ሲመለከት የነበረው የሀረሪ ክልል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ28ቱም ተከሳሾች ላይ ከ1 አመት ከ8 ወር እስከ 2 አመት ድረስ በእስር እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *