
የአውስትራሊያ ጠ/ሚ ስኮቲ ሞሪሰን ዛሬ ማለዳ እንደተናገሩት ከሆነ የኮሮና መነሻ የት ነው የሚለው ምክንያታዊ በሆነ መልኩ ሊጠና ይገባል ብለዋል፡፡
አውስትራሊያና ቻይና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዚሁ ጉዳት የተነሳ በመካከላቸው ቅያሜ ገብቷል፡፡
ጠ/ሚ ሞሪሰን የኮሮና ቫይረስ እንዴት ሊከሰት ቻለ በሚለው ላይ ምርመራ ይደረግ ሲባል ቻይናን ለማሳጣት አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከ 2ሺ በላይ ሰዎችን ህይወት የነጠቀው የኮሮና ቫይረስ በቻይና ውሃን በሚገባ ላብራቶሪ ውስጥ ተሰርቶ የወጣ ነው የሚል አሉባልታ መኖሩ ቻይናን ሲያስቆጣ የቆየ ጉዳይ ነው፡፡
በአውስትራሊያ 6,738 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሪፖርት የተደረገ ሲሆን 88 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡