መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 22፣2012-አጫጭር መረጃዎች

~ የግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሲልከን ቫሊ መሪ ኢለን ማስክ ሰዎች በቤታቸዉ እንዲቀመጡ መገደዳቸዉ ዲሞክራሲን የሚገዳደር ፋሺስታዊ አካሄድ ነዉ ሲል ተቹ፡፡በአንጻሩ የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከንበርግ ክልከላዎችን በአፋጣኝ ለማንሳት የሚደረገዉ ጥረት ስጋት እንደሆነበት ተናግሯል፡፡

~ በጀርመን የሚገኙ ሙዚየሞች፣ቤተ ክርስቲያኖች እና የእንስሳት ማቆያ በድጋሚ ሊከፈቱ ነዉ፡፡ጥብቅ መመሪያን በመተግበር ዳግም እንደሚከፈቱ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርኬል አስታዉቀዋል፡፡

~ በስፔን መዲና ማድሪድ ዜጎች በአፓርታማ ቤታቸዉ በረንዳ ላይ በመሆን በስክሪኖች ፊልም መከታተል ጀምረዋል፡፡በሰኔ ማብቂያ የባህር ዳርቻ ስፍራዎች ለህዝብ ክፍት እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

~ በሀንጋሪ ትምህርት ቤቶች እስከ ግንቦት መጨረሻ ዝግ ሆነዉ ይቆያሉ ተባለ፡፡

~ በእንግሊዝ ለንደን ከተማ በኮሮና የጥቁሮች የሞት መጠን ከነዋሪዎች መጠን አንጻር አለመዛመዱ ተነገረ፡፡በለንደን ከሚኖረዉ ህዝብ የጥቁሮች ድርሻ 13 በመቶ ቢሆንም በቫይረሱ በለንደን የሞቱት የጥቁሮች ብዛት ግን 16 በመቶ ነዉ፡፡ለዚህም የተሰጠዉ ምክንያት ተጋላጭ ስፍራዎች ላይ ስራን ለመስራት ጥቁሮች ስለተገደዱ ነዉ ተብሏል፡፡

~ በስፔን ከስድስት ሳምንታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፉት 24 ሰዓት ዝቅተኛ ሞት ተመዘገበ፡፡በ24 ሰዓት ዉስጥ የ268 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 24,275 ደርሷል፡፡

~ በኢንዶኔዥያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ10ሺ ልቋል፡፡በተመሳሳይ በማሌዥያ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ6ሺ በላይ ደርሷል፡፡

~ በአሜሪካ የስራ አጦች ቁጥር 30 ሚሊየን መድረሱን መንግስት አስታወቀ፡፡ባለፈዉ ሳምንት ብቻ 3.8 ሚሊየን አሜሪካዉያን ስራ የለንም ሲሉ አመልክተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *