
የፓኪስታን ፓርላማ አፈ ጉባኤ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸዉ ተነገረ
አፈ ጉባኤዉ ፋይሰል ኢዲህ በሳምንቱ መጀመሪያ ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚንስትር ኢምራሃን ካሃን እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣት ጋር ግንኙነት የነበራቸዉ መሆኑን ተከትሎ ስጋት ተፈጥሯል፡፡ባሳለፍነዉ ሰኞ በነበረ ፖለቲከኞች በተገኙበት የአፍጥር ስነስርዓት ላይ አፈ ጉባኤዉ ተገኝተዉ ነበር፡፡
በፓኪስታን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 16,817 ሲደርስ የ385 ሰዎች ህይወት ደግሞ ቀምቷል፡፡